የባለ አክኪዮን ውክልና እንደራሴነትቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

Bunna Insurance (S.C)

የቡና ኢንሹራንስ አ/ማኅበር የባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣370 እና 393 እንዲሁም በኩባንያው መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 8፣ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 4 እና 6 መሰረት የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ህዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ባለአክሲዮኖች በእለቱ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስልተላልፋል፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎች

I/ የ8ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
 2. የጉባዔውን ፀሐፊ መሰየም፣
 3. በድምጽ ቆጣሪዎች ውጤት መሰረት ምልዓተ ጉባዔ መገኘቱን በንግድ ህጉ መሰረት ማረጋገጥ፣
 4. የዕለቱን የስብሰባ አጀንዳ ማጽደቅ፣
 5. በኩባንያው ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችንና አዲስ አክሲዮን ሽያጮችን መቀበል፣
 6. እ.ኤ.አ የ2020/2021 የዳይሬክተሮች ቦርድን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
 7. የቀረበውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 8. እ.ኤ.አ የ2020/2021 የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
 9. የቀረበውን የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 10. እ.ኤ.አ የ2020/2021 የተጣራ ትርፍ ድርሻ ላይ የቀረበውን ውሳኔ ኃሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 11. ከ7ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ የተተኩ የቦርድ አባልን ተቀብሎ ማጽደቅ፣
 12. እ.ኤ.አ በ2022 ለሚመረጡ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር 48/2020 መሰረት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት መሰየም፣
 13. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሻሻለ መመሪያ ቁጥር SIB/46/2018 መሰረት እ.ኤ.አ የ2020/2021 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ እና እ.ኤ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርኃዊ አበል መወሰን፣
 14. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፣

II/ የ5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
 2. የጉባዔውን ፀሐፊ መሰየም፣
 3. በድምጽ ቆጣሪዎች ውጤት መሰረት ምልዓተ ጉባዔ መገኘቱን በንግድ ህጉ መሰረት ማረጋገጥ፣
 4. የዕለቱን የስብሰባ አጀንዳ ማጽደቅ፣
 5. በማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 6. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፣

III/ ማሳሰቢያ፣

 • በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ህጋዊ ውክልና በመስጠት ወይም ከስብሰባው ሦስት ቀናት በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የውክልና ፎርም በመሙላት በወኪል አማካኝነት በስብሰባው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል፡፡
 • ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎች ወደ ስብሰባ ቦታው ሲመጡ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናው እና ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • በጤና ጥበቃ ኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት ማንኛውም የስብሰባ ተሳታፊ ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 • ለባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የተዘጋጁ ሰነዶችን ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም ህጋዊ ወኪል ስብሰባው ከሚካሄድበት ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ከኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ማርኬቲንግ መምሪያ ቢሮ መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የባለ አክኪዮን ውክልና ፎርም እንደራሴነት ለማግኘት ይህንን ይጫኑ 

ቡና ኢንሹራንስ አ/ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Language