ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ለመተከል ተፈናቃዮች 250 ኩንታል ዱቄት እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን አበረከተ

ሀገራዊ ኢኮኖሚን አንድ እርምጃ ወደ ፊት ለማራመድ ራዕይ ሰንቆ የተመሰረተው ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ጥር 4 2013 ዓ.ም ጥቅል ዋጋቸው 650,000 ብር የሚያወጡ 250 ኩንታል ዱቄት እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመተከል ተፈናቃዮች አበርክተዋል። የቡና ኢንሹራንስን በመወከል እርዳታውን ያስረከቡት የቡና ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዘውዱ ሚናስ እና የኢንሹራንሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳኛቸው ማህሪ ናቸው፡፡ እርዳታውን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል “ድጋፉ በቂ ሆኖ ሳይሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሰባዊነት የሚሰማው ሁሉ የአንድ ቀን ቁርሱን ቢለግስ የተራቡ ወገኖቻችንን ምሳ እና እራት ከመመገብ አልፎ ማቋቋም የሚችል አቅም መፍጠር እንችላለን ስለሆነም ሌሎች ባንኮችና ኢንሹራንሶች እንዲሁም ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተቋማት እና ግለሰቦች ለእነዚህ ግፉአን አለኝታቸውን በተግባር ሊገልፁ ይገባል መሰረታችን ህዝብ ነውና ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Language